ፍቅር የሚያሲዝና ያማረ ዓይን፣ ያለሜካኘ
ተፈጥሮ ያሳመረው ዓይን ጤናማ ከመሆኑም በላይ በትንሽ ሜካኘ እጅግ ያማረ ዓይን ይኖርሻል። የሚከተሉትን ሞክሪ እስኪ በደንብ እረፍት ውሰጅ ፦ የእንቅልፍ እጥረት ካለብሽ ሰውነትሽ ራሱን የማደሻ ጊዜ ስላላገኘ ማሳመር ይከብዳል። ወደ አይንሽም በበቂ ሁኔታ ደም ስለማይመላለስ የቀላና የደረቀ ዓይን ይሆናል። የአይን ቅንድብሽን ተቀንደቢ፦ በስሱ ብቻ ተቀንደቢ፣ የተቀረፀና ፀጉር ያለው ቅንድብ ለዓይንሽ ፍሬም ሆኖ ውበቱን ያጎላሉ። አይንሽ ጎልቶ እንዲወጣ ወደ ላይ መቦረሽ ትችያለሽ። የቅንድብ ቅርፅሽ ከፊትሽ ቅርፅ ጋር መጣጣሙንም አረጋግጪ። በዓይንሽ ዙሪያ ያለውን የሠውነት ቆዳ ጠብቂ ፦ በዓይንሽ ዙሪያ ያለው ቆዳ ስስ ስለሆነ በክሬምና በመሳሰሉት እንድትንከባከቢ ዶክተሮች ይመክራሉ። በቂቤ ወይም በኩከምበርና በመሳሰሉት መንከባከብ ትችያለሽ። ማታ ማታ ሁልጊዜ የዓይንሽን ዙሪያ ክሬም ቀቢ፦ ይህ ዓይንሽ የተዋበ እንዲሆን ይረዳል ምክንያቱም የተጎዳ ቆዳሽ ስለሚታደስ። ዓይንሽ ያብጣል ጠዋት ጠዋት? ፦ የሄ የሚመጣው አለርጂክ የሆነብሽን ምግብ ተመግበሽ ወይም ደግሞ በቂ እንቅልፍ ስላላገኘሽ ይሆናል። ስለዚህ መጀመሪያ በቀዝቃዛ ውሃ ፊትሽን ታጠቢ፣ በኩከምበር ወይም በሻይ ቅጠል መንከሪያ ወይም በትንሿ የሻይ መንኪያ በስሱ የዓይንሽን ዙሪያ ጫን ጫን አድርጊ። የዓይን ሽፋሽፍትሽን ወደ ላይ አዙሪው ፦ ከርል ያደረግሽው ሽፋሽፍት ከዓይንሽ መስመር ጋር ትይዮ እንዲሆን አድርጊ። ጤንነትሽ በጥሩ ሁኔታ ይጠበቅ፦ ጤናሽ ሲጠበቅ ዓይኖችሽ ያበራሉ ስለዚህ በስፖርት ወይም በእንቅስቃሴ የታጀበ ህይወት ይኑርሽ።